top of page

የማህበረሰቡን ደህንነት መጠበቅ።

ለህብረተሰቡ ደህንነት ቅድሚያ ለመስጠት ቁርጠኛ ነኝ። የሃገሪቱ ቦርድ አባል እንደመሆነ ለደህንነት ቅድሚያ የሚሰጡ ፖሊሲዎችን ለመቅረጽ እሰራለሁ፤ ወንጀል ቅነሳ ላይና የሁሉም ሰው ደህንነትና የተካታችነት ስሜት የሚሰማበትን ቦታዎች ለመፍጠር እሰራለሁ። ህበረተሰቡን የሚያጋጥሙትን ተግዳሮኦች ለመፍታት፣ ወንጀልን ለመከላከልና የማህበረሱን ደህንነት የሚያራገግጡ ፕሮግራሞች ላይ እንቨስት በማድረግ የቀደሚነት ሚና እወስዳለሁ።

Kids Blowing Bubbles

ደህንነታቸው የተጠበቁ ቦታዎች ለወጣቶች: እንደ አንድ የአርልንግተን ነዋሪና እንደ ሁለት ልጆች እናት የማህበረሰቤ  በተለይም የወጣቶች ደህንነትና ህልውና ያሳስበኛል። ለዛ ነው ለህጻናት ትምህርት ቤት በማይሆኑበት ጊዜ የሚሄዱበትን ሰላማዊ የሆኑ ቦታዎች ለመፍጠር እድሎችን ለመፍጠር ጠንክሬ ለመስራት ቁርጠኛ የሆንኩት።  በህብረተሰብ ማእከላት በሚሰሩ ፕሮግራሞችና ግብአቶች ላይ እንቨስት በማድረግ በወጣቶች ላይ የሚፈጸሙ የህገ ወጥ እጽ አጠቃቀምና እና ወንጀልም መቀነስ እንችላለን። በጣም ወጣት ከሆኑ ነዋሪዎች አንስቶ የእያንዳንዱን ህብረተሰብ ነዋሪ ህይወት ለማሻሻል ለመስራት ተሰጥችያለሁ።

ወጣቶችን ማዘጋጀት: በሌሎች የህብረተሰቦች ነገሮች ላይ ያተከሩ ስራዎች ለልጆች የሚጠቅሙ ፕሮግራሞች ላይ እንዳንሰራ እንዳጠሉብን አስተውያለሁ። እንደ አንድ ለወጣቶች የልብ ተቆርቋሪ  የወጣት ማህበረሰብ አባላትን ፍላጎት ለማስቀደም እዋጋለሁ። እያንዳንዱ ህጻን ሰላማዊና በተለያየ መንገድ በሚረዱ ቦታዎች እድገቱንና ልማቱን የሚያጎለብቱ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ፕሮግራሞች ማግኘት አለበት ብዬ አምናለሁ። ለወጣቶች ደህንነታቸው የተጠበቁና አሳታፊ የሆኑ ፓርኮች፣ መዝናኛና ስፖርታዊ ፕሮግራሞች አቅርቦት የመጨመር እንቅስቃሴ የዛ ተልእኮ አካል ነው። የወጣት ስራዎችን ተቀዳሚ በማድረግ ወንጀሎችን መቀነስና ለሚመጣው ትውልድ ብሩህ የሆነን ወደፊት መፍጠር እንደሚቻል አምናለሁ። በትክክለኛ ግብአቶችና መሪነት በመላው ማህበረሰባችን ህልውና ላይ ትርጉም ያለው ተጽእኖ ማምጣት እንችላለን።

እጽ ላይ ያለውን እውቀት የማሳደግ እንቅስቃሴ: የእጽ ሱስ ቤተሰቦችንና ማህበረሰቦችን የመበተን አቅም አለው። እና ለዛም ባለኝ አቅም ሁሉ ይሄን ነገር ለመከላከል ቁርጠኛ ሆኜ የምሰራው።  የእጽ ትምህርትን  ቅድሚያ ለመስጠትና ማህበረሰቡን በተለይም ወጣቶችን ስለ እጾች አደገኛ ባህሪ እንደ ድኢኤው ‘አንድት የእጽ እንክብል ትገድላለች’ እንቅስቃሴ ለማስተማር እንቅስቃሴ ለማስጀመር እሰራለሁ። በጋራ በመስራት ሱሰኝነትን መከላከል እንችላለን፤ ደግሞም ሁሉም ነዋሪዎቻችን ደስተኛና ጤናማ የሆነ ህይወትን እንድኖሩ የምያስፈልጉ ነገሮች ሁሉ ማድረግ እንችላለን። በዚህ እንቅስቃሴ ላይ ተቀላቀሉኝ። በጋራ እንቁምና ለእጾች እንቢ እንበልና ለጤናማ ጉልበተኛ ማህበረሰብ እሺ እንበል።

የምክር አገልግሎት: ለረጅም ጊዜ በአርልንግተን እንደ ኖረ ሰው የህዝቡን እምቅ አቅምና ክንውናቸውን በሚገባ አውቃለሁ። እንደ ሃገሪቱ የቦርድ አባል ተቀዳሚ ግቦች ብዬ ካልኳቸው ውስጥ ወጣቶች ከስኬታማ የህብረተሰብ አባላት ድጋፍና መሪነት የሚያገኙበትን የምክር አገልግሎት ማስጀመር ነው። ይህ ፕሮግራም ለቀጣዩ የአርልንግተን ትውልድ ፍላጎቶቻቸውን እንድከተሉ የመሰረት ድንጋይ ይሆናል።

የመድሃኒት ህክምና: በጣም አሳሳቢ ከሆኑ ከሚያጋጥሙን ነገሮች አንዱ የእጽ መንሰራፋት ነው። ትምህርት ቤቶቻችን ላይ የምታየው እጽን ከመጠን በላይ መጠቀምና እጽን በመጠቀም የሚከሰቱ አደጋዎች ቁጥር በጣም እየጨመረ ይገኛል። ዝም ብለን በመቀመጥ ይሄ ነገር እንድሆን መፍቀድ የለብንም። እንደ ሃገራችሁ ቦርድ አባል እንደመሆነ ይሄን ነገር ፊት ለፊት ለመጋፈጥ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳልል እሰራለሁ። የእጽ መንሰራፋት ላይ አርልንግተን የማያዳግም እርምጃ እንድትወስድ ጊዜው አሁን ነው። ግለሰቦች የእጽ ሱስን ለማቆም የሚታከሙበትን የማገገሚያ ማእከል ብሎም ወጣቶችን የሚጠቅሙ ፕሮግራሞች የሚደረጉበትን ቦታዎች ለመክፈት ምን አልባትም ባዶ ህንጻዎች በመለወጥ ለመስራት ቃል እገባለሁ። እጽን ለመጠቀም የሚዳርጉ መሰረታዊ ምክንያቶች ለማግኘትና ለችግሮቹ አዳዲስ መፍቲሄዎች ለማምጣት ከወላጆች፣ ከአስተማሪዎች፣ ለትርፍ ካልቆሙ ድርጅቶቸና ከሌሎች የማህበረሰብ አባላት ጋር እሰራለሁ። በጋራ ማህበረሰባችንን ለመኖር ጤናማና ደህንነቱ የተጠበቀ ማድረግ እንችላለን።

የአእምሮ ጤና አገልግሎቶች: በአእምሮ ጤና ላይ እንቨስት ማድረግ በነዋሪዎቻችን ጤና ላይ እንቨስት እንደማድረግ ነው። የኔ ፖሊሲዎች ማንኛውም ሰው ደስተኛና ጤናማ ህይወት ለመኖር እድል ይገባዋል የሚል እምነት አላቸው። የአእምሮ ጤና በማህበረሰባችን ደህንነት ላይ ያለውን ትልቅ ተጽእኖ በሚገባ እረዳለሁ፤ እና ለዛም ነው ለተሻሉ ግብአቶችና አገልግሎቱን ለምሹ አቅርቦቱን ለማሳደግ የምሰራው።

ከህግ በላይ የሆነ መተባበርና ስልጠና: የድኤምቪ አካባቢ የተስተዋለው የመኪና ስርቆት፣ ዘረፋዎች፣ ጥቃቶችና ስርቆቶች በአቅራቢያችን ካሉ አካባቢዎች ጋር እነዚህን የጋራ ችግሮች ለማቆም የጋራ ስታራቴጂ እንድናበጅ አስገዳጅ ሆነዋል። ይሄም በተለያዩ አካባቢዎች የሚከሰቱ ችግሮች ለመከላከል የተለያዩ በብዙ አካባቢዎች የሚሰራ ግብረ ሃይል ማቋቋም እና የልምምድ ስልጠናዎችና ስትራቴጂ መቀየስን ያካትታል። በተለያዩ ኤጀንሲዎች፣ በህግ አስፈጻሚ አካላትና ማህበረሰቦች መካከል ያለውን መቀናጀትና መተባበር በማሳደግ እነዚህን ተግዳሮቶች ለመቀነስና አካባቢያችንን ለነዋሪዎች ሰላማዊ ለማድረግ እሰራለሁ።

ለድንገተኛ አገልግሎቶች የገንዘብ ድጋፍ: እንደ ሃገር እያደግን ስንመጣ ለድንገተኛ አገልግሎቶች ቅድሚያ መስጠት ለምሳሌ ፖሊስ፣ የእሳት አደጋ ሰራተኞችና ለመጀመሪያ መላሾች አስፈላጊ ነው፤ ሁሉም በዚህ ጊዜ ከሚያስፈልጋቸው የሰራተኛ ቁጥር በታች ይዘዋል። አንደኛው አማራጭ የኮሌጅ ድግሪ ላላቸው በደረጃ እድገት ወይም የደመወዝ ጭማሪ በማድረግ የትምህርት እድል ማዘጋጀት ነው።  እንደ ሃገሪቱ ቦርድ አባል ከጎረቤት አካባቢዎች አካላት ጋር በሚስማማ መልክ ለድንገተኛ ጊዜ ሰራተኞች ክፍያ ለማምጣት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳልል እሰራለሁ፤ በጣም ምርጥ የሆኑትን ለመመልመልና በአካባቢዎች ለማስቀረት ነው።

የተማሪዎች ብድር ይቅር ማለት ወይም ለሰራተኞች የክፍያ እርዳታ ማድረግ: የፖሊስ መርማሪዎች ለማስቀረት ብልጥና ውጤታማ መንገዶችን ለማግኘት በቁርጠኝነት እሰራለሁ። ከዚህም አንደኛው የማደርገው መንገድ የተማሪዎች ብድር ይቅር በማለት ወይም የክፍያ እርዳታ ፕሮግራም በመስጠትና በሱ ፋንታ በኤሲፕድ ወይም በፖሲስ መስሪያ ቤት መስራት እንድቀጥሉ በማድረግ ነው። ይሄም አማራጭ የተማሪ ብድርን እዳ ለሰራተኞች ይቀንሳል፤ በዛውም ልምድ ያካበቱና የተሰጡ የፖሊስ መርማሪዎች በማህበረሰባችን እንድቆዩ ያደርጋል።

bottom of page