top of page

መግባባትና ግልጸኝነት

የእንቅስቃሴዬ ማእከላዊ ሃሳብ ክፍትና ግልጸኛ መንግስት መመስረት ነው። መንግስት ክፍትና ግልጽ ሲሆን ሁሉም ሰው ተጠቃሚ ይሆናል ብዬ አምናለሁ። ነዋሪዎች መንግስት የነሱን ፍላጎት ከግንዛቤ ባስገባ መልኩ ዉሳኔዎችን እንደምያስተላልፍ ይተማመናሉ ደግሞም የመንግስት ሰራተኞች ከነዋሪዎች እይታ ጥሩ ግብአት ማግኘት ይችላሉ። ለሃገሪቱ ቦርድ ከተመረጥኩኝ ሃገሪቱ ግልጽና ስነ_ምግባርን በጠበቀ መልኩ እንድትቀሳቀስ ባለኝ አቅም ሁሉ እሰራለሁ።

ስልታዊ እቅድ

ስለ አርልንግተን ነገ ራእይ ማርቀቅና ያንን ለማሳካት እድግ ማውጣት

አርልንግተን ለመኖር፣ ለመስራትና ለቤተሰብ በጣም አስደናቂ ቦታ ነው ግን ደግሞ እያደግንና እየተለወጥን ስንሄድ የሚመራን እቅድ መኖር አስፈላጊ ነው። ራእይና ስልታዊ እቅድ ለማህበረሰብ የረጅም ጊዜ ስኬት ቁልፍ ጉዳዮች ናቸው። ያለ ራእይ ወዴት እንደምንሄድ አናውቅም። ያለ ስልታዊ እቅድም መሪ እንደሌለው መርከብ ነን።የኔ ተልእኮ የማህበረሰባችንን ተግዳሮቶችን በመቅረፍ ጥንካሬዎቻችንን የሚያጎለብቱ ስልታዊ እቅዶች ላይ ከአርልንግተን ህዝብ ጋር በጋራ በመሆን መስራት ነው። በእያንዳንዱ ውሳኔዎቻችን ውስጥ ግቦቻችንና ምኞቶቻችን እንድንጸባረቁ ለማረጋገጥ እሰራለሁ።

ጎረቤትን ያማከለ ግንኙነት

መኖሪያ አካባቢያቸውን የምመለከቱ ጉዳዮች ላይ የአካባቢው ነዋሪዎች እንድያውቁ  እፈቅዳለሁ።

ለረጅም ጊዜያት የአርልንግተን ነዋሪዎች በአካባቢያቸው ስለምሆኑ ነገሮች ምንም ነገር እንዳያዉቁ ተደርገው ቆይቷል፤ በሌላ በምንም ምክንያት ሳይሆን ከሃገሪቱ ድህረገጽ ላይ መረጃ ማግኘት ከባድ ስለሆነ ብቻ ነበር። እንደ ሃገሪቱ የቦርድ አባልነቴ ይሄን ለመቀየር ቁርጠኛ ነኝ።  ለግንኙነት የምጠቀመው ዘዴ ቀለል ያለ ነው፤ ይህም አካባቢ ተኮር፣ ግልጽና ለማግኘት ቀላል የሆነ ማለት ነው። ከዚህ በኋላ ነዋሪዎችን ከውሳኔ አሰጣጥ ሂዴት ዉጪ የሚያደርግ ለሁሉም አንድ መጠን አሰራር አይኖርም። እኔ ለያንዳንዱ ነዋሪ ለአርልንግተን ነገ ድምጽ የምሆንበትን እድል መስጠት እፈልጋለሁ፤ አና ደግሞም ይሄ የምጀምረው ነዋሪዎች በአካባቢያቸው ስለምሆኑ ነገሮች እውቀት ስኖርቸው ነው።

በህዝባዊ አስተያየቶች ላይ ግልጸኝነት

የፖሊሲ ውሳኔዎችን የፌደራል መንግስት ህዝባዊ አስተያየቶችን ለአዳዲስ ደንቦች እንደሚያስተናግዳቸው መያዝ።

እናንተን ለማገልገል እንደተመረጠ እንደ አንድ ግለሰብ ተቀዳሚ ከማደርጋቸው ጉዳዮች መካከል የመጀመሪያው የህዝቦች ድምጽ እንድሰማና ፍላጎታቸው እንድሟላ ማድረግ ነው። ይሄን ለማድረግ ግልጸኝነት ቁልፍ ነው ብዬ አምናለሁ፤ እና የተሻለ አካታችና ግልጸኝነት ያለበት የውሳኔ አሰጣጥ እንድኖር ለማድረግ ቁርጠኛ ነኝ።ይሄ ማለት የህዝብ አስተያየቶች የፌደራል መንግስት ለተሰጡ አዳዲስ ደንቦች የምከተለውን ሂደት በሚመስል መልኩ ክፍት በሆነ መንገድ ይገመገማሉ። የህዝቡን ግብረመልስ ከተቀበልን በኋላ የተሰጡት አስተያየቶችና በውሳኔ አሰጣጡ እንዴት ከግንዛቤ እንደገቡ ይታተማል። የአርልንግተን ነዋሪዎች ድምጻቸው እንደተሰማና ሃሳባቸው ዋጋ እንዳለው ሊያውቁ ይገባል።

የመረጃ ነጻነት ህግ ስራዎች

ማንኛውም ከሁለት ጊዜ በላይ የተጠየቀ ጉዳይ በሃገሪቱ ድህረ ገጽ ላይ መታተም አለበት።

ተጠያቂነት የየትኛውም መንግስት ግንባር ቀደም ጉዳዮች መሆን አለባቸው። ለዛ ነው እንደ ሃገሪቱ የቦርድ አባልነቴ ማንኛውም በመረጃ ስራ ነጻነት ከሁሉት ጊዜ በላይ የተጠየቀ የመንግስት ሰነድ በሃገሪቱ ድህረገጽ ላይ እንድታተም ለመስራት እዋጋለሁ ያልኩት። ህዝባችን እነዚህን ሰነዶች የማግኘት መብት አለው፤ ያንን እውን ማድረግ ደግሞ የኔ ሃላፊነት ነው።

ስልታዊ እቅድ

bottom of page