top of page

የኔ ታሪክ

አያቴ ናት ያሳደገችኝ። እንደ ቤቱ አስተዳዳሪ፣ ከበደል የዳነችና ለአራት ሴቶች እናት እንደመሆኗ እሷ ለኔ መነቃቂያዬ ናት። እንግልዝኛ ለማይናገሩ ወላጆች ስለተወለደች ለአስር ወንድምና እህቶች ስትል ትምህርቷን ለማቋረጥ ተገደደች። ልጅነቷ በድህንነት ነበር።  እንደ ጎልማሳ የምግብ ባንኮችን ለመጎብኘት ስትሄድና በእጅ የተጨማደዱ ልብሶችን መልበስ ምን ያህል እንደምታፍርና ስሟ አሜሪካዊ ስላልሆነ ብቻ ይደርስባት የነበረውን መድሎ ታስታውሳለች።  እሷ ላይ የደረሰው ነገር ሁሉንም ሰው በክብርና በርህራሄ ማየት እንዳለብኝ፣ ልክ ባልሆነ ነገር ላይ በድፍረት እንድናገርና ነገሮችን ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለ ለማድረግ መስራት እንዳለብኝ ውስጣዊ ፍላጎት ጭሮብኛል። ከጥቅት አመታት በፊት በ103 አመቷ በሞተች ጊዜ ያጽናናኝ ነገር ያንን ረጅም እድሜዋን እያንዳንዱን ቀን በቅንነት፣ በርህራሄና ተስፋ ባለመቁረጥ መኖሯ ነው። እሷ የተወለደችው በ1919 ነው፤ ያ አመት ሴቶች የመምረጥ መብት የተሰጣቸው አመት ነበር። ዛሬ ላይ እሷ ያሳደገቻት የልጅ ልጇ መምረጥ መቻል ብቻ ሳይሆን ለመመረጥ እሷ ራሷ የተጠቀማቻቸውን የመሪነት መርሆች ተጠቅማ ተስፋን ሰንቃለች፣

IMG_7856.jpeg
IMG_1685.jpg

ዩሊዬ ለአርልንግተን እንቅስቃሴ በእያንዳንዱ ሰው ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ነው። ለረጅም ጊዜ ነዋሪ እንደመሆነ፣ APS ላይ ለተመዘገቡ ሁለት ልጆች እናት እንደመሆነ፣ ለትንሽ ቢዚነስ ባለቤት እንደሆነ ሰውና እንደ አንድ ቁርጠኛ የህብረተሰብ አባል አርልንግተን ለሁሉም ነዋሪዎቿ በሚጠቅም መልኩ እንድታድግ ከልብ እመኛለሁ። ለዚች ሃገር ያለኝ ራእይ እድገትን ከዘላቂነት ጋር ማስተባበርን የያዘ ሲሆን ይሄን ሲል የአርልንግተንን ለመኖርና ለመስራት ልዩ የሚያረጋትን ለየት ያለ ሞገስና ባህሪ ሳይለቅ ማለቴ ነው። አዳዲስ ሃሳቦችን ለመተግበር፣ አዳዲስ ፈጠራዊ መፍቲሄዎች ለማየትና ሁሉም እንድያድግ እድሎችን ለመፍጠር ከማህበረሰቤ ጋር ለመስራት ቁርጠኛ ነኝ።

የማህበረሰቤን ደህንነትና ብልጽግና ለማረጋገጥ ትኩረት እሰጣለው።  የህዝብ አገልጋይ እንደመሆነና በተለያዩ የፌደራል መንግስት ከሃገር ውስጥ ደህንነትና ከአሜሪካ ካፒቶል ፖሊስ ጋር ለሁለት አስርት አመታት እንደሰራ ሰው ለማገለግለው ህዝብ ግልጸኛና ተጠያቂ መሆን ጥቅሙ ምን ያህል እንደሆነ በሚገባ እረዳለሁ። እኔ አርልንግተን ለመኖርና ለመስራት ድንቅ ቦታ ሆና እንድትቀጥልና የማህበረሰቡን ደህንነት ለማረጋገጥ ቅድሚያ ሰጥቼ እሰራለሁ። የተለያዩ ትላልቅና የብዙ ሚሊየን በጀት ያለቸውን ፕሮጄክቶች የማስተዳደር ልምድ ስላለኝ ይሄን የኛን ማህበረሰብ መጠቀም በሚገባው ልክ መጠቀም እንድችል ለመስራት ክህሎቱና ልምዱ እንዳለኝ በራሴ እተማመናለሁ።

በሃገሪቱ ቦርድ አባል እንደመሆኔ እያንዳንዷን ቀን ለሚሰሩ ቤተሰቦችና የንግድ ስራ ባለቤቶች ለመዋጋት እሰራለሁ። በጋራ አርልንገተንን የነቃችና የበለጸገች ሆና ለመጪው ትውልድ እንድትቆይ ማድረግ እንችላለን።

IMG_2267_edited.jpg

Let’s Work Together

Get in touch so we can start working together.

  • Facebook
  • LinkedIn
  • Instagram
  • Youtube
  • X
bottom of page