ብልህ እቅዶችና እድገት
የህብረተሰባችን የተሻለ ነገ የምጀምረው እዚሁ የምኖሩ ሰዎች ከመስማት ይጀምራል ብዬ አምናለሁ። እኔ ከሁሉም የአርልንግተን ነዋሪ ጋር የኛ ጥልቅ እሴቶችና ተቀድሚ ጓዳዮች ላይ የጋራ ራእይ ለመፍጠር ለመስራት በጣም ቁርጠኛ ነኝ። ለእድገትና ልማት የምጠቅሙ ለህብረተሰብ ቅድሚያ የሚሰጡ ብልህ መንገዶችን በመጠቀም አርልንግተን ለመኖር፣ ለመስራት እና ወደ ፊት የሚመጣው ትውልድ ድንቅ ቦታ እንድትሆን ማረጋገጥ እንችላለን።
ተግባራዊ መፍትሄዎች
መኪና ማቆሚያ
ሃገሪቱ ለሜትሮ ጣቢያው ¾ ማይል ላይ ለተገነቡ 50% ቤቶች ብቻ የመኪና ማቆሚያ እንድኖር ማዘዟን ታውቃላችሁ? ይህ በቂ አይደለም። የተለያዩ የግል ምንጮች እንደጠቆሙት ከ60_65% በህዝብ መጓጓዣ አገልግሎት አጠገብ የሚኖሩ ሰዎች መኪና አላቸው። ይሄን እውነታ ቸል ማለት አንችልም። ይሄ የመኪና ማቆሚያ ወጪዎችን ክፍያ በጣም ከፍ ያደርገዋል። ይሄም ከፍ ካለው የቤት ክራይ ዋጋ ጋር አንድ ላይ በአርልንግተን መኖርን በጣም ከባድ ያደርገዋል። ከሜትሮ ኮሪደር ውጪ የመኖሪያ ቤቶችን ቁጥር ከመኪና ማቆሚያዎች ጋር ባልተመጣጠነ መልኩ መጨመር መኪኖች መንገድ ዳር እንድቆሙና መተፋፈግ እንድከሰትና የትራፊክ ፍሰትን ያስተጓጓላሉ። ከዚህች ሃገር የመኪና ማቆም ፖሊሲ የሚጠቀሙት ብቸኛው አካል የፖሊሲ አርቃቂዎች ናቸው፤ እና ይሄ ደግሞ ማህበረሰቡን ይጎዳል። እንደ ሃገሪቱ የቦርድ አባል ሁሉንም ሰው ተጠቃሚ የሚያደርጉ መፍቲሄዎች ለማምጣት እዋጋለሁ።
ሽፋን
የአርልንግተን ነዋሪዎች የህዝቡ ቁጥር ስጨምር ወሳኝ ወቅት ላይ ናቸውና እኛ አርልንግተን ለመኖር ምቹና ተፈላጊ ቦታ እንድትሆን ወጥረን እንሰራለን። እንደ ሃገር ቦርድ ተወካይኔቴ የመሬት አጠቃቀምና ልማት ጋር የተገናኙ ጉዳዮች ላይ መስራት ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው። ሃገሪቱ ከዚህ በፊት የተተገበሩ ለውጦች በህብረተሰቡ ላይ ያመጡትን እውነተኛ ተጽእኖ ስልታዊ በሆነ መንገድ መገምገም አለባት ብዬ አምናለሁ። እንደገናም ደግሞ የልማት የረጅም ጊዜ በደን ሃብት፣ በአረንጓዴ ስፍራ፣ በአየር ንብረትና በጎርፍ ውሃ ላይ የሚያመጣውን ተጽእኖች ወደፊት ለሚመጣው ትውልድ ጤናማና ደስ የሚል ከባቢን ለማስጠበቅ ይሄን ከግምት ማስገባታችንን ማረጋገጥ አለብን።
ሁለንተናዊ መንገድ
አርልንግተን ለመኖር አንደናቂ ስፍራ ናት ይሁን እንጂ እንደ ህብረተሰብ እያደግንና እየተለወጥን ስንመጣ የተለያዩ ተግዳሮቶችን እንጋፈጣለን። እንደ ሃገሪቱ የቦርድ አባልነቴ ማንኛውም አይነት የልማት ስራ ወሳኝ መሰረተ ልማቶችን ለምሳሌ ትምህርት ቤቶችን፣ ድንገተኛ ጊዜ አገልግሎቶች፣ የጎርፍ አደጋና የሃይል አገልግሎትን ከግምት ማስገባታቸውን ለማረጋገጥ ቁርጠኛ ሆኘ እሰራለሁ። እነዚህ ጉዳዮች ሁላ ላይ የሚታሰቡ ሊሆኑ አይችሉምና ግን እስከ ዛሬ እንደዚህ ነበር ሲሰራ የነበረው። እነዚህ ወሳኝ ጉዳዮች ቸል ማለት በተለይም ለተሻለ ነገ የምናቅድ ከሆነ አንችልም።
ከቤተሰብ ቁጥር የሚመጣጠን ቤት
ከተማ ላይ ቤት ከመግዛቴ በፊት ለብዙ አመታት በአርልንግተን ተከራይቻለሁ። ወደዚህ የመጣሁበት ምክንያት ስንኖርበት የነበረው አፓርታማ የቤተሰቤ ቁጥር በጨመረ ጊዜ ስላልበቃን ነበር። ህብረተሰባችን እያለፈበት ካሉ ችግሮች መካከል ዋነኛው ከቤተሰብ ቁጥር ጋር የሚመጣጠን ቤት እጥረት ነው። ከ70% በላይ የአርልንግተን መኖሪያ አፓርታማዎች እና ኮንዶምኒየን ነው፤ ሰፋ ያለ ቦታ ለምፈልጉ ቤተሰሶች ትንሽ ቦታ ይቀራል። እኛ አሁን የሁሉንም ሰው ደህንነቱ የተጠበቀና ከህዝቡ አቅም ጋር የሚምስማሙ ከቤተሰብ ቁጥር የሚመጣጠኑ ቤቶችን ማልማት ላይ ትኩረት ማድረግ አለብን ብዬ አምናለሁ። ለሁሉም የአርልንግተን የተሻለ ነገን ለመፍጠር በማደርገው እንቅስቃሴ ተቀላቀሉኝ።
የንግድ ሪል እስቴት ክፍት የስራ ቦታዎች
የሃገሪቱን ኢኮኖሚ፣ የንግድ ስራዎችና ነዋሪዎች ተጠቃሚ የሚያደርጉ የንግድ ሪል ስቴት ክፍት የስራ ቦታዎች መፍትሄዎች ለማግኘት ከልቤ ለመስራት ዝግጁ ነኝ። ባዶ የሆኑ የንግድ እቃዎች ወደ ቤት ወይም ሌሎች ጥቅም ወደ ሚሰጡ ለመለወጥ፣ አዳዲስ የንግድ ስራዎች ወደ አካባቢው ለመሳብና የክፍት ስራ ቦታዎች በነዋሪዎች ግብር ያለው ተጽእኖ ለመቀነስ በጀቱን ለመገምገም ቁርጠኛ ነኝ። የሚበልጽግ ሃገራዊ እኮኖሚ ሁሉንም ተጠቃሚ ያደርጋል ብዬ አምናለሁ ደግሞም አርልግተንንን የበለጸገች ለማድረግ በንቃት እሰራለሁ።